ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 16/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለእንስሳት ዝርያ ማሻሻል የሚያግዝ የፈሳሽ ናይትሮጅን ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ።
በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የፈሳሽ ናይትሮጂን ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያ እና ማሰራጫ ማዕከል በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
በምረቃው ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የአርሶና አርብቶ አደሩን እንስሳት ዝርያ በማሻሻል ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፥ የናይትሮጅን ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከሉ እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ማዕከሉ በክልሉ ካለው የእንስሳት ሀብት ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፥ ከዚህ ቀደም ይነሳ የነበረውን የእንስሳት ዝሪያ ማዳቀያ ግብዓት ችግር እንደሚፈታም ተናግረዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ማዕከሉ በክልሉ ያለውን የእንስሳት ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የአርሶና አርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያሳድጋል ብለዋል።
በተለይ የክልሉ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ተግባሩን በማሳደግ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማሳለጥም የማዕከሉ ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንም አስረድተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይም የክልሉና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025