ድሬዳዋ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ኢኮኖሚን የሚያነቃቁና በአርአያነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ተናገሩ።
ሀላፊው በድሬዳዋ አስተዳደር በግንባታ ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት፣ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማምረቻ ሼዶች፣ የኮንቬንሽን ማዕከል እና በመደመር መፅሐፍ ሽያጭ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን ዘመናዊ ቤተ መጻህፍት ተመልክተዋል።
በአስተዳደሩ የተመለከቷቸው የልማት ፕሮጀክቶች የድሬዳዋን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የህዝብን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ ገልጸው፣ በአርአያነት የሚጠቀሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በድሬዳዋ የለውጡ አመራር የጋራ ህብረትና መደጋገፍ እንዲሁም የነዋሪው የተቀናጀ ተሳትፎ እየተመዘገቡ ለሚገኙ አበረታች ውጤቶች መሰረታዊ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።
ከልማቱ በተጨማሪ በድሬዳዋ እየተፈጠረ ያለው የጋራ ገዢ ትርክትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት በአርአያነት የሚጠቀስ መሆኑንም ተናግረዋል።
በድሬዳዋ በተለያዩ መስኮች እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ይበልጥ ሲጠናከሩ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያሳድጉታልም ነው ያሉት።
በልማት ሥራዎች ጉብኝት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025