አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ዲጂታል ማንነት ወሳኝ መሆኑን የአይዲ ፎር አፍሪካ ሊቀ መንበር ጆሴፍ አቲክ(ዶ/ር) ገለፁ።
ዲጂታል ማንነት ላይ ያተኮረው አይዲ ፎር አፍሪካ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአይዲ ፎር አፍሪካ ሊቀ መንበር ጆሴፍ አቲክ(ዶ/ር)፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ታድመዋል።
የአይዲ ፎር አፍሪካ ሊቀመንበር ጆሴፍ አቲክ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው።
የዛሬው ቀን የአፍሪካውያን የዲጂታል ማንነትን ለማረጋገጥ ጉዞ የምንጀምርበት አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በጉባኤው ለልማት መታወቂያ፣ አይዲ 4 (ID4) እንቅስቃሴን በተመለከት ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲወጣ የምናስገነዝብበት ነው ብለዋል።
የአፍሪካ መሪዎች የዓለምን ተለዋዋጭ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግንባታ ትኩረት ሰጥተው ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም አመልክተዋል።
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሽግግርን እውን ለማድረግ ዲጂታል ማንነትን ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአፍሪካ ዲጂታል ማንነት ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ልማትና የዜጎች ኑሮ ለማሻሻል ወሳኝ ሚና እንዳለው ነው ያስታወቁት።
ይህ መድረክ የወደፊቷን ዲጂታል አፍሪካ ለማረጋገጥ ሁሉም አፍሪካዊ ማንነቱን ለማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የምናሳይበት ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025