ባህርዳር፤ ግንቦት 9/2017(ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰላምን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ የተለያዩ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
በከተማው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ49 ሽህ 300 ለሚበልጡ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉም ተመልክቷል።
የባህር ዳር ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 29ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ባለው መድረክ ምክትል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የዘጠኝ ወራት የስራ ክንውን ሲያቀርቡ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
በዚህም ሰላምን አፅንቶ ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የተከናወኑ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያጎለብቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአስፋልት ግንባታን ጨምሮ የኮሪደር ልማት፣ የከተማ ግብርና እና አረንጓዴ ልማት ምክትል ከንቲባው ከጠቀሷቸው ተግባራት መካከል ይገኙበታል።
በተጨማሪም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ49ሺህ 376 ሰዎች በአገልግሎት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች የስራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል።
የወጣቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በሚካሄዱ የሰላም ግንባታና የልማት ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተረዋል።
የባህር ዳር ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አዲስ ትርፌ፤ ህገ ወጥ ነጋዴዎች የሚፈጥሩትን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
የምክር ቤት አባላት ስራ አስፈጻሚው ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር እያከናወነው ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴዎች በመከታተል እየደገፉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የባህር ዳር ከተማን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል የአካባቢውን ሰላም በጋራ ተደራጅቶ በመጠበቅ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጠል አስገንዝበዋል።
በባህር ዳር ከተማ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቃናት በሚቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ ልዩ ልዩ ረቂቅ ደንቦችና መመሪያዎችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025