አዲስ አበባ፤ግንቦት 8/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ ልማት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ዲጂታል መሰረተ ልማትን እያስፋፋች ነው ሲሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመድአ) ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ።
በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በዚሁ ወቅት፤ ቴክኖሎጂ አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባትና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የማይተካ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታውን በቅጡ በመገንዘብና ቴክኖሎጂ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ያለውን ፋይዳ በመረዳት ዲጂታል መሰረተ ልማትን እያስፋፋች መሆኗን አስታውቀዋል።
ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና ኢኒሼቲቭ እንዲሁም የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፥ ይህም ዜጎች ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ የመኖር መብታቸውን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
ኤክስፖው እንደ ሀገር ብሎም እንደ አህጉር ቴክኖሎጂን ማዕከል አድርገው የተሰሩ ስራዎችና የዕድገት ደረጃውን በተመለከተ የሚመከርበትና ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦች የሚፈልቁበት ነው ብለዋል።
አስተዳደሩ የሳይበር ደህንነት ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ ቁልፍ የመሰረተ ልማት ተቋማትን ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሳይበር ደህንነት ካውንስል ሊቀ መንበር መሃመድ አልኩዋቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ቴክኖሎጂ ዓለምን የመቀየር ትልቅ አቅም እንዳለው አንስተዋል።
የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ብሄራዊ ደህንነትንና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ላይ ሀገራት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ ትብብርን ማጠናከርና ተለዋዋጭ የሳይበር ደህንነት ስጋትን ታሳቢ ያደረገ አቅም መገንባት ወሳኝ እንደሆነም ጠቁመዋል።
የቴክኖሎጂ ኤክስፖው እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ የበርካታ ሀገራት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና ከአስር ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን አንድ ላይ አገናኝቷል።
በኤክስፖው ከፍተኛ ተቀባይነትና ዕውቅና ያላቸው ከመቶ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ ጀምረዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025