የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አመርቂ ስኬት አስመዝግቧል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ

May 16, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንባት 7/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ስኬት ማስመዝገቡን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።


ለሁለት ቀናት የሚቆየው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል።


በፎረሙ ላይ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የባንክ የስራ ኃላፊዎች፣ የዓለም አቀፍ የገንዘብና የልማት አጋር ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።


የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፥ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ዕድሜ ያለው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን ያህል ዕድገት ሳያስመዘግብ መቆየቱን አውስተዋል።


በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ የነበሩ መሰናክሎችን ለማለፍም አካታችና ዘመኑን የዋጀ ሥርዓት የሚፈጥር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል።


የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ በተደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።


በቀጣይም የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር ቀጣይነት ያለው ስራ እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል።


የኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ለዘርፉ አንገብጋቢ ችግሮች ምላሽና መፍትሔ አመላካች ምክረ ሃሳቦችን በመስጠት የግሉን ዘርፍ ለማነቃቃት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አስረድተዋል።


የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዓለም አቀፍ ድጋፍና ዕውቅና ማግኘቱን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.