አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2017(ኢዜአ)፦ በኢንቨስት ኢትዮጵያ 2025 ፎረም ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና በኢትዮጵያ ያሉ ሰፊ ዕድሎችን በማስተዋወቅ በኩል ስኬታማ ስራ መከናወኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአጋር የልማት ድርጅቶች አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2025 ፎረም ተጠናቋል።
በመድረኩ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በፎረሙ ከበርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ የሚያስችል ውይይትና መግባባት መፈጠሩ ተገልጿል።
በዚሁ መሰረትም አምስት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መጀመር የሚያስችላቸውን ስምምነት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራርመዋል።
ኩባንያዎቹ በማዕድንና ሌሎችም ዘርፎች ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ተነግሯል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፎረሙ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሀገር መሆኗ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና በኢትዮጵያ ያሉ ሰፊ እድሎችን በማስተዋወቅ በኩል ስኬታማ ስራ መሰራቱንም ጠቁመዋል።
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ይዞ የመጣቸው እድሎች ላይ በቂ ግንዛቤ መፈጠሩን ተናግረው፤ በቀጣይም በዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በበኩላቸው ፎረሙ የታለመለትን ዓላማ ያሳካ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘርፉ እድገት የሚያግዙ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ማሻሻያዎችም በመድረኩ በስፋት ማስተዋወቅ መቻሉን አንስተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025