የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ሰላምን በማፅናት በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል- ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ

May 13, 2025

IDOPRESS

ባህርዳር፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የተገኘውን ሰላም በማፅናት በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕስ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ።


የክልሉ የመንግስት አመራር አባላት በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ በባርዳር ከተማ የውይይት መድረክ እያካሄዱ ነው።


ዛሬ በተጀመረው የውይይት መድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንዳመለከቱት፤ በክልሉ የተከናወነው የህግ የበላይነት የማስከበር ተግባር ውጤታማ ነው።


በዚህም ሰላምን በማፅናት በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸው፤ ይህም መሰረተ ልማትን በመገንባት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን በማከናወን እንደሆነ አስታውቀዋል።


በቀጣይም የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በየደረጃው ያሉ አመራር አባላት እስካሁን ሲያከናውኑ ከቆዩት በላቀ ደረጃ በቁርጠኝነት መትጋት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።


በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ በበኩላቸው፤ ፅንፈኛውን ቡድን ከክልሉ በማፅዳት ልማትን በዘላቂነት የማስቀጠሉ ተግባር መጠናከሩን ተናግረዋል።


በክልሉ የፀናውን ሰላም በማስቀጠል የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነቱን ይበልጥ ለማጎልበት በየደረጃው ያለው አመራር አበክሮ መስራት እንዳለበት አሳሰበዋል።


በውይይት መድረኩ በየደረጃው ያሉ አመራር አባላት እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.