ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በማዕድን ዘርፍ 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ መሰጠቱን የክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ኃይሌ አበበ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ የማዕድን ሃብትን በአግባቡ በማጥናትና በማልማት ከዘርፉ የሚጠበቀውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት እየተሰራ ነው።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኮንስትራክሽን ማዕድን ልማት ለመሰማራት 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ ጥያቄ ላቀረቡ 4ሺህ 326 ባለሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል።
በከፍተኛ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ የኮንስትራክሽን ዘርፍና በባህላዊ ማዕድን ምርት ለተሰማሩ ባለሃብቶች ፍቃዱ መሰጠቱን ነው የተናገሩት።
ቢሮው በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በካርታ የተደገፈ የማዕድን ክምችትና ልየታ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች እያካሄደ መሆኑንም አመልክተዋል።
የማዕድን ክምችት፣ አይነትና መጠንን ከመለየት ባለፈ የተገኙ ማዕድናትን በማስተዋወቅ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በመሳብ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በዘጠኝ ወራት በተከናወኑ የማዕድን ፍለጋና ግመታ ጥናቶች ከታቀደው 80 በመቶ የሚሆነውን ማሳካት መቻሉንም ተናግረዋል።
በጥናቱ የኮንስትራክሽን፣ የኢንዱስትሪ፣ የኢነርጂ፣ ብረት ነክ እንዲሁም የከበሩና በከፊል የከበሩ ማዕድናትን በመለየት ለማዕድን ኢንቨስትመንት ምቹ የማድረግ ሥራ መሰራቱን ቢሮ ሀላፊው አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025