ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦ በህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየውን የልማት ቁርጠኝነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት በሌሎችም መስኮች ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር) ገለጹ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር የግድቡን አሁናዊ ሁኔታና የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀምን በተመለከተ ከጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር) እንዳሉት በግድቡ ግንባታ የታየውን ብሔራዊ አንድነት በሌሎች የልማት መስኮች በመድገም የሀገርን እድገት ማፋጠን ይገባል።
የህዳሴ ግድብ ግንባታ ወደ መጠናቀቅ ምዕራፍ እየተቃረበ መሆኑን ገልጸው፤ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የክልሉ ህዝብና መንግስት ሲያደርግ የቆየውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር በበኩላቸው የግድቡ ግንባታ የኢትዮጵያውያንን አንድነት በተግባር ያሳየ ታሪካዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
እንደ ሀገር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለግድቡ ግንባታ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን ገልጸው የግድቡ ግንባታ ቀሪ ስራ እስኪጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
የጋምቤላ ክልል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ሃላፊ ኮማንደር ጋትቤል ቦል በበኩላቸው በክልሉ በበጀት ዓመቱ ለግድቡ ግንባታ 10 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ ሲሰራ መቆየቱን አመልክተዋል።
እቅዱን ለማሳካትም በቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራት ጊዜ ውስጥ ያልተቋረጠ ርብርብ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
በውይይቱ መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025