ሀዋሳ፤ ሚያዚያ 16/2017(ኢዜአ):- በሲዳማ ክልል የቡና ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በሸበዲኖ ወረዳ ፉራ ቀበሌ ተጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ እንደገለጹት፤ በክልሉ ከ29 ሚሊዮን በላይ የተሻሻለ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።
ሙሉ ፓኬጅን በመጠቀም ወደ ተከላ የተገባው በክልሉ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማጠናከር መሆኑን አመልክተዋል።
በባህር ዛፍ የተያዘ ሰፊ መሬትን ነጻ በማድረግ የቡና ልማት ላይ እንዲውል እየተደረገ መሆኑን አውስተዋል።
ይህም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚረዳ ገልጸዋል።
በዚህም ከባህር ዛፍ ነጻ የተደረገን ጨምሮ ከ11ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ተከላ እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ፋንታዬ ከበደና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025