አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 15/2017(ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የማህበራዊ ልማት ዘርፍ የሰው ሀብት ልማት እና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ክንውኖችን ገምግሟል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማው ወቅት እንደገለፁት፥ በክልሉ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
በተለይ የትምህርት እና ጤናው ዘርፍ ጤናማ፤ብቁ፤ክህሎት ያለው እና አምራች ዜጋን ማፍራት ቁልፍ ስራቸው አድርገው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
በጤናው ዘርፈው በሽታን መከላከል ብሎም አክሞ ማዳንን መሰረት ያደረገ ስራ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በሌላ በኩል በትምህርት ዘርፍ ሐረር በ12ኛ ክፍል የማሳለፍ ምጣኔ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በተለይ ባለፈው ዓመት ሁሉም የከተማ እና ገጠር ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ችለዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የተመዘገበውን ውጤት ማስፋት ይገባል ብለዋል።
የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥን ማስቀረት እና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እንደሚገባም አክለዋል።
በሌላ በኩል የክልሉ ህዝብ የጋራ ባህል፤ታሪክ እና ማንነት ያለው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አብሮነት እና ወንድማማችነትን ይበልጥ የሚያጎለብቱ የወል ትርክትን የሚያሰርፁ ተግባራትን በትኩረት ማከናወን ይገባል።
በተለይ ወቅቱን የዋጀ የባህል ልማት ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ ብቁ፤ነፃና ገለልተኛ የሲቪል ሰርቪስ በመፍጠር ልዩነት የሌለበት፤ፍትሀዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተጀመረውን ውጤት ማስፋት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አመራሩም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ቁልፍ ስራው አድርጎ በመውሰድ ከማህበረሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን በዕቅድ ይዞ መፍታት ይጠበቅበታል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025