አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 15/2017 (ኢዜአ)፦የጎንደር ከተማን ሥምና ዝና ለመመለስ እየተከናወነ ላለው የመልሶ ግንባታ ልማት "ኑ ጎንደርን እንሞሽር" በሚል መሪ ሀሳብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሊካሄድ መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቀረበ።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ቻላቸው ዳኛው በሰጡት መግለጫ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማን የቀደመ ስምና ዝና ለመመለስ የመልሶ ግንባታ እና መሰረተ ልማትን የማሟላት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የከተማዋን መልሶ ግንባታ በማስጀመር የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶች እንዲታደሱ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ለዓመታት ደብዝዞ የቆየው የጎንደር ገጽታ መፍካቱን ነው የጠቀሱት።
የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ኢትዮጵያውያን የድርሻቸውን እንዲወጡ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።
የጎንደርን የትንሳኤ ጉዞ ማሳካት አለብን ያሉት አቶ ቻላቸው፥ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ጎንደርን በማልማት ስራ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ያለመ መሆኑንም አንስተዋል።
በመሆኑም በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የሚገኙ የጎንደር ተወላጆች፣ መላው ኢትዮጵያውያን፣ የዓለምአቀፍ ተቋማትና ኤምባሲዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025