የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰቶ ይሰራል-ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

Apr 23, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2017(ኢዜአ):-የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰቶ ርብርብ እንደሚደረግ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በሐረሪ ክልል የሴክተር መስሪያ ቤቶች የ 2017 የ 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በዛሬው ዕለት መካሄድ በጀመረው ግምገማው በኢኮኖሚ ልማት ዘርፎች ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ተገምግመዋል።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተድር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማ መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰቶ ርብርብ ይደረጋል።

ከማህበረሰቡ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ገቢን በተገቢው መንገድ ሰብስቦ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ልማቶች በማዋል ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም ገልፀዋል።

በተለይ በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን በአግባቡ አልምቶ በመጠቀም ገቢ ማመንጨት እና ሀብት መፍጠር እንደሚገባ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።

በመሆኑም በገቢ አሰባሰብ ሂደት ሲስተዋሉ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ተሰብሳቢ ገቢዎችን በቁርጠኝነት መሰብሰብ ቀዳሚ ስራ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ ምርታማነትን በማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት የገበያ ዋጋን በተወሰነ ደረጃ በማረጋጋት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።

ምርታማነትን ከማሳደጉም በላይ አርሶ አደሩ እራሱን በምግብ ከመቻል አልፎ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ የኢክኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በቀጣይም ምርታማነትን በማሳደግ የተመዘገበውን ውጤቶ ለማስፋት ትኩረት ሰቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ የኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሻለ መነቃቃት መኖሩን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎች በጊዜ ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

በስራ ዕድል ፈጠራ የተሰራጨውን ብድር የማስመለስ ስራም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ጋር በተገናኘም አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በተያዘላቸው ግዜ ስራቸው ያልተከናወኑ ቀሪ ፕሮጀክቶችን ከጥራት፤ግዜና እና ዋጋ አንፃር በመፈተሽ የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በቀጣይም በግምገማ መድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን መነሻ ያደረገ የማካካሻ ደዕቅድ በማዘጋጀት በዕቅድ ተይዘው ሳይከናወኑ የቀሩ ተግባራትን በቀሪ ግዜያት ማከናወን እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.