የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የግብርና ልማት ባለሙያዎችን የማብቃት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል

Apr 11, 2025

IDOPRESS

መቀሌ፤ ሚያዝያ 2/2017 (ኢዜአ)፡- በትግራይ ክልል የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግየግብርና ልማት ባለሙያዎችን የማብቃት ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ገለፀ።

የክልሉን የ2017/18 የምርት ዘመን እቅድ ለማሳካት የቅድመ ዝግጅትና የመኸር ወቅት የግብርና ልማት የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ በክልሉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ዛሬ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ከደነው እንደገለፁት በአዝርእት፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ውጤታማ ስራ በመስራት የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ የባለሙያው ሚና የማይተካ ነው።

የክልሉን ምርታማነት ለማሳደግ የግብርና ባለሙያዎች ችግሮችን ተቋቁመው ለአርሶ አደሩ እየሰጡ ላሉት ሙያዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና በዘርፉ እየተገኘ ያለውን ለውጥ ለማጠናከር ባለሙያውን በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ እየተከናወነ ያለው የማብቃት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በኩታ ገጠም ልማት፣ በግብርና ሜካናይዜሽን ማስፋት፣ በገበያ ተኮር ምርት እንዲሁም በሌሎች የእርሻ ፓኬጅ ስራዎች ሙያዊ የቴክኒክ አጠቃቀም ዙሪያ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና እንደሚሰጥ አቶ አበራ ገልፀዋል።

በክልሉ በ2017/18 የምርት ዘመን ከሚታረሰው መሬት ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን በክላስተር /በኩታ ገጠም ዘዴ/ ለማልማት እቅድ ተይዟል ብለዋል።

በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች አዲሱ የግብርናና ገጠር ፖሊሲን በማስተዋወቅና ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባራዊ ስራ ለመቀየር ዝግጅት መደረጉን ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

ከሰልጣኞቹ መካከል ወይዘሮ ፍሬህይወት ገብረየሱስ ስልጠናው አርሶ አደሩን ለመደገፍ የሚያስችል ተጨማሪ አቅምን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይ የምርታማነት ማሳደጊያ ዘዴዎች፣ የእርሻ ፓኬጅ፣ በሰብል ምርታማነት፣ በእንስሳት ሀብት እና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስልጠና መሰጠቱ በባለሙያዎች መካከል የተቀናጀ ትብብር እንዲኖር ያስችላል ያሉት ደግሞ ከማይጨው ወረዳ አቶ ሀጎስ በላይ ናቸው ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.