አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2017(ኢዜአ)፡- የፈጠራ ውጤቶች የክህሎት ባንክ እንደሀገር ለተጀመረው የክህሎት ልማት መስፈንጠሪያ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።
በሰመር ካምፕ እና በክህሎት ኢትዮጵያ መርኃ ግብር የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶች የክህሎት ባንክ ትናንት ተከፍቷል።
ባንኩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል መርቀው ከፍተውታል።
ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ በባንኩ የሚገኙት የፈጠራ ውጤቶች በባለፈው ዓመት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም እንዲሁም በዘንድሮ የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚገኝበት ነው።
የክህሎት ባንክ የቴክኖሎጂ ባለቤቶችን የፈጠራ ምርቶችን መጠቀምና ማስመረት ከሚፈልጉ ደንበኞች ጋር የሚያገናኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ባንኩ ለጎብኚዎች ክፍት ሲሆን የመንግስት እና የግል ዘርፉ የፈጠራ ውጤቶችን በመጎብኘት እንዲመረትላቸው የሚፈልጓቸውን የቴክኖሎጂ ምርትች ትዕዛዝ መስጠት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል።
ይህ ለሀገሪቱ የመጀመሪያው የሆነው የክህሎት ባንክ ለክህሎት ልማት ትልቅ መስፈንጠሪያ እንደሚሆንም ነው ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የገለጹት።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ21 ኢንተርፕራይዞች ያዘጋጀው የመስሪያ ቦታ ርክክብ ተደርጓል።
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) ርክክብ የተደረገው የፈጠራ ሀሳብን ወደ ተግባር ለቀየሩ ስራ ፈጣሪዎች ነው ብለዋል።
የማሽነሪና በቀላሉ ድጋፍ አግኝተው ወደ ገበያ መውጣት ለሚችሉ የስራ ፈጠራዎች ርክከብ መደረጉን ነው የገለፁት።
የቦታ ርክክብ የተደረገላቸው የፈጠራ ባለቤቶች የሆኑት እሱባለሁ አለልኝ እና አህላም አሊ ድጋፉ የፈጠራ ስራቸውን በስፋት ለመስራት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025