አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች ነው ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ የልማት ዳይሬክተር ፖል ዋልተርስ የተመራ ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እንዲሰማሩ ቁልፍ ማሻሻያዎች ተደርገዋል - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች መሆኗንና ከመቼውም ጊዜ በላይ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበናል ሲሉ ለልኡካን ቡድኑ መግለጻቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ሚስተር ፓል በበኩላቸው ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ እያሳየች ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል ሲሉም ገልጸዋል።
ለአለም ንግድ ድርጅት አባልነት እያደረግን ያለውን ዝግጅትም አድንቀዋል ብለዋል።
በሁለትዮሽ የገበያ ዕድሎች ዙሪያ በቀጣይነት በጋራ በምንሰራባቸው አግባቦች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ሲሉም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025