አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ሀብቶችን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለመቀየር በትኩረት ይሰራል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቀጣይ ሶስት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተጀምሯል።
እቅዱ የክልሉን የልማት አቅምና ጸጋ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ ያሉ ተፈጥሯዊና ሰብአዊ ሀብቶችን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለመቀየር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ለእቅዱ መሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሰሩም አሳስበዋል።
በመድረኩ እቅዱን አስመልክቶ በሚቀርቡ ሰነዶች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025