ቁሊቶ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ):- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠንካራ የሕብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በሀላባ ዞን "የተዋሃዱ ህብረት ስራ ዩኒየኖች ለሁለንተናዊ ብልፅግና "በሚል መሪ ሀሳብ የዩኒየኖች የውህደት መድረክ ተካሂዷል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ስሩር በወቅቱ እንዳሉት መንግስት የህብረት ስራ ማህበራት አደረጃጀቶችን በማጠናከር ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የሪፎርም ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የክልሉ ህብረት ስራ ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ውጤት ከማስመዝገብ አኳያ በርካታ ጉድለቶች ያለባቸው መሆኑን ተከትሎ በአዲስ መልክ ሪፎርም ማድረግ ማስፈለጉንም ጠቁመዋል፡
ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ በግብይት ስርዓት ውስጥ የሚስተዋለውን ችግር በመፍታትና የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡
በክልሉ ጠንካራ የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይም የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ተመስገን ጎዴቦን ጨምሮ የዞኑ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የህብረት ስራ ማህበራት አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025