ደብረ ማርቆስ፤ የካቲት 17/2017(ኢዜአ)፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰላምን ከማጽናት ጎን ለጎን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የዞኑ መስተዳድር አስታወቀ።
የዞኑ መስተዳደር ባለፉት ሰባት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በደብረማርቆስ ከተማ ገምግሟል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ በወቅቱ እንዳሉት በወረዳና በቀበሌዎች በርካታ ህዝባዊ መድረኮችን በማዘጋጀት ከማህበረሰቡ ጋር በመምከር ሰላምን የሚያጸኑ ተግባራት ተከናውነዋል ።
በዚህም ከ51ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ብለዋል።
በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ መቀነስ እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል።
ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚከናወኑ የሰላምና የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል ።
የዞኑ የትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በበኩላቸው የተገኘው ሰላም በማህበራዊ ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን ተቀናጅተን ለመፍታት አስችሎናል ብለዋል።
አሁን ላይ ተማሪዎች ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መውሰድ የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የማህበረሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ የተሰራው ስራ አበረታች ለውጥ አምጥቷል ያሉት ደግሞ የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ አበባው በለጠ ናቸው።
ህብረተሰቡን በማስተባበር የመጣውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በግምገማ መድረኩ የዞኑ መስሪያ ቤቶች ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላትተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025