የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>ኮርፖሬሽኑ በ742 ሚሊዮን ብር የሚያስገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓት ማዕከል እየተጠናቀቀ ነው</p>

Jan 21, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ ፤ጥር 12/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ742 ሚሊዮን ብር የሚያስገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓት ማዕከል እየተጠናቀቀ መሆኑን ገለጸ።

የኮርፖሬሽኑ የስራ ሀላፊዎች የተቀናጀ የግብርና ግብዓት ማዕከሉን ግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ አቶ ካሳሁን ከበደ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ ግብርና ዘርፉን በማዘመን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያግዙ ግብአቶችን እያቀረበ ነው።

ከዚህም ባለፈ ተደራሽነቱን ለማስፋት በሀገር ደረጃ የቅርንጫፎችን ቁጥር መጨመሩን ገልፀው ግብርናውን የሚያዘምኑ ማሽነሪዎች፣ ምርጥ ዘርና የአግሮ ኬሚካል ግበዓቶችን ለአርሶ አደሮችና በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች እያቀረበ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በአብነትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በ742 ሚሊዮን ብር የተጀመረው ለምርጥ ዘር ማከማቻ፣ ለመጋዝንና ለቢሮ አገልግሎቶች የሚውል ባለ አራት ወለል የተቀናጀ የግብርና ግብዓት ማዕከል ህንጻ ግንባታ 98 በመቶ ደርሷል ብለዋል፡፡


እስካሁንም የምርጥ ዘር ማበጠሪያና ማዘጋጃ ማሽን ተከላው እየተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የግንባታ አካልም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የምርጥ ዘርና ደን ውጤቶች ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘነበ ወልደሥላሴ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ የግብርና ስራውን የሚያዘምን የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ተደራሽነት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡


በዚህም ከመሬት ዝግጅት ጀምሮ እስከ ጎተራ ድረስ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን እያቀረበ ግብርናው እንዲዘምን እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮርፖሬሽኑ የዘር ብዜቱን ከራሱ በተጨማሪ በሰፋፊ የባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ማሳ ላይ እንደሚያከናውን ተናግረው በ2016/17 የምርት ዘመን 464 ሺህ ኩንታል በላይ የተለያየ አይነት ምርጥ ዘር እንደሚያሰራጭ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.