አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ204 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለወጪ ገበያ በመላክ ከ908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ ከቡና ውጪ ንግድ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል።
በዚህም ወደ ውጭ ከተላከው ከ204 ሺህ 206 ቶን ቡና ውስጥ ባለፉት ስድስት ወራት 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኙቱን ተናግረዋል።
ይህም በዕቅዱ አንጻር 127 በመቶ ብልጫ ያለው ገቢ መሆኑን ጠቁመው፤ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 571 ሚሊየን ጋር ሲነጻጻር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይ ወራትም የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025