አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ):- በሐረሪ ክልል የኮሪደር ልማት ስራዎች በተሻለ ፍጥነት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።
አቶ ኦርዲን በዚሁ ወቅት እንዳሉት የኮሪደር ልማት ስራው በተሻለ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።
በተለይም በከተማው በ1 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ በተሻለ ፍጥነት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ከግንባታው ስራ ጎን ለጎን እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የአባድር ፕላዛ አካባቢውን ባማከለ መልኩ ከዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ጋር በማስተሳሰር እየተከናወነ እንደሚገኝና የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጨምር በማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው አመራሩ የራሱን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025