የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ከግሉ ዘርፍ ያለውን ትብብር የማጠናከር ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል -በለጠ ሞላ (ዶ/ር)</p>

Jan 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ከግሉ ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የመግባቢያ ስምምነቶችን ከግሉ ዘርፍ ተቋማት ጋር ተፈራርሟል።

ስምምነቱ ከሳይበር ዘብ ኮንሰልቲንግ ፣ከኮርፖ መረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ( ICTET) የዘርፍ ማህበር እንዲሁም ኑና ኢትዮጵያ ከተሰኙ የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች ጋር የተከናወነ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፈጠራ ስራን ለማበረታታት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የግሉ ዘርፍ ተቋማት የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፈጠራ ግቦችን ለማሳካት ስምምነቱ የራሱ ፋይዳ አለው ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ካሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ዘላቂ የሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመፍጠር፣ የዘርፉን እድገትን ለማሻሻል እና የማይበገር የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለመገንባት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ ስምምነቶቹ የግሉ ዘርፍ ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና በፈጠራ ቀጣናዊ መሪ ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ ጉልህ እርምጃ እንዲኖራቸውና በንቃት እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.