የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ ስለአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) ምን አለች?

Jan 13, 2025

IDOPRESS

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ለአፍሪካ እና አፍሪካውያን ያላትን መሻት አንጸባርቃለች። በዚህም፦

በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከአፍሪካ ህብረት እና አባል ሀገራት ጋር በቅርበት እንደምትሰራ፤

የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) ግቦችን የሚያሳኩ የተለያዩ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች እየተገበረች መሆኑን፤

የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) ማዕቀፍ የግብርና ምርታማነትንና የምግብ ዋስትናን ለማሳደግ እንዲሁም ዘላቂነት ላለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቀቃም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ፤

የአየር ንብረት ለውጥ፣ የህዝብ እድገት፣ የከተሜነት መስፋፋት እና አሁን ላይ የሚታዩ ዓለም አቀፍ ቀውሶች በግብርናው ዘርፍ ላይ የጋረጠውን ፈተና በውል መገንዘብ እንደሚገባ፤

የካዴፕ ግቦችን ለማሳካት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት የተለያዩ ብሔራዊ ኢኒሼቲቮች እየተገበረች መሆኑን፤

በብሔራዊ ስንዴ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት ዓመታዊ የስንዴ ምርቷ ወደ 23 ሚሊዮን ቶን ማደጉንና ይህም ሀገሪቱ ለ50 ዓመታት ከውጭ ስታስገባ የቆየውን ስንዴ በራሷ አቅም እንድታመርት እንዳስቻላት፤

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ስድስት ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በመተከላቸው የደን ሽፋኑን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉን፤

የሌማት ትሩፋት የእንስሳት ምርታማነትን ማሻሻልና በተለይም የዶሮ፣ የወተት፣ የአሳ፣ የስጋና የማር ምርታማነት እንዲጨምር ማድረጉንና ይህም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ለማሳደግ አስተዋጽኦ ማበርከቱን፤

በአጠቃላይ ኢኒሼቲቮቹ ከምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን፤

ግብርና ለአፍሪካ ከዘርፍነት ባለፈ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥነት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ኑሯቸውን የሚመሩበትና ለዘላቂ ልማት ትልቅ አበርክቶ ያለው መሆኑን፤

በአፍሪካ የማይበገር እና ዘላቂነት ያለው የግብርናና የምግብ ስርዓት ለመገንባት ለተያዘው ራዕይ ስኬታማነት ኢኖቬሽን፣ አካታችነት እና ዘላቂነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ፤

የግብርና እና የምግብ ስርዓቶችን ለአደጋዎች እና ለፈተናዎች የማይበገር ለማድረግ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ ብዝሃ የምርት ስርዓትን መፍጠር እና በማህበራዊ ሴፍቲኔት ላይ ሙዓለ ንዋይ በማፍሰስ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍ እንደሚያስፈልግ፤

በአፍሪካ ትውልድ ተሻጋሪ የምግብ ዋስትናንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የበለጸገች አህጉር ለመፍጠር የጋራ ትብብርና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈለግ አጽንኦት ሰጥታ አንጸባርቃለች።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.