ባሌ ሮቤ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ እያካሄደ ለሚገኘው የግብርና ቆጠራ መረጃ አሰባሰብ ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲጠናከር ጠየቀ።
አገልግሎቱ ከባ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና በሮቤ ከተማ እየሰጠ ነው።
በአገልግሎቱ የቢዝነስ ታትስቲክስ መሪ ሥራ አስፈፃሚ እና የሁለቱ የባሌ ዞኖችና የምዕራብ አርሲ ዞን የግብርና ቆጠራ የክላስተር አስተባባሪ አቶ ናቃቸው ነጋሽ እንዳሉት፣ የስታትስቲክስ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርና ናሙና ቆጠራ ማካሄድ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
አገልግሎቱ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሙያዎችን መልምሎ ካሰለጠነ በኋላ ወደ መስክ በማሰማራት ተጨባጭ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።
በሁለቱ የባሌ ዞኖችና ከፊል የምዕራብ አርሲ ዞን የተውጣጡ 833 የሚሆኑ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ወስደው የመስክ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።
የቤተሰብ ምዝገባና መረጣ፣ የሰብል ምርትና ምርታማነት ግምገማ፣ የእንስሳት ቆጠራ ሥራዎች እስከ አሁን ከተከናወኑ ሥራዎች መካከል ናቸው።
ከሁለቱ የባሌ ዞኖች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ባለድርሻ አካላት ስለ ግብርና ቆጠራው ጥልቅ ግንዛቤ ኖሯቸው ለመረጃ አሰባሰቡ ውጤታማነት እገዛ እንዲያደርጉ ለማነሳሳት ነው።
ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የባሌ ጎባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አሰፋ በበኩላቸው፣ የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ሥልጠና በግብርና ቆጠራው ፕሮግራም የጠራ መረጃ በማሰባሰብ ለሚፈለገው ሀገራዊ ዓላማ እንዲውል እገዛ እንዲያደርጉ ያግዛል ብለዋል።
በስካሁኑ ሂደት ከግንዛቤ እጥረትና ሌሎች በዘርፉ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲፈቱ እገዛው ከፍተኛ መሆኑንም አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በ2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ሁለተኛው ዙር የግብርና ናሙና ቆጠራ ለበርካታ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱን የአገልግሎቱ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025