ሰመራ/ሀዋሳ/ሀረሪ ጥር 1/2017(ኢዜአ):- መንግስት ያመቻቸውን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መከታተል በመቻላቸው ስራቸውን በተሻለ መልኩ ለማከናወን እያገዛቸው መሆኑን ከአፋር፣ ከሲዳማና ከሀረሪ ክልሎች አስተያየታቸውን የሰጡ ሰልጣኝ ወጣቶች ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ መርሃ ግብር ለወጣቶች ታላቅ እድል መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።
ወጣቶች በመርሃ ግብሩ ለመሳተፍ በመመዝገብ የክህሎት ባለቤት በመሆን ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲያገኙ ሁሉም እንዲያበረታታ ጥሪ ማቅረባቸውም እንዲሁ።
ሰልጣኞቹ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ወጣቶች በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ከሚፈጠሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ራሳቸውን በፍጥነት እንዲያራምዱ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወሳኝ ነው፡፡
በአፋር ክልል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያ የሆነው ወጣት ሻምበል መሐመድ እንደገለፀው፤ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን መከታተሉ ስራውን በተሻለ መልኩ እንዲያከናውን አስችሎታል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ መስራት ዘመኑ የሚጠይቀውና ተመራጭ መንገድ መሆኑን ገልፆ፤ መንግስት ባመቻቸው ዕድል መጠቀም ደግሞ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጋር መገናኘት የሚያስችሉ ክህሎት ባለቤት መሆን ነው ብሏል።
በሲዳማ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ባለሙያ ወጣት ሮቤል ዳንኤል፤ በኢትዮ ኮደርስ ከሚሰጠው ስልጠና አራቱንም ኮርሶች ማጠናቀቁን ተናግሯል፡፡
የዓለም የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደት እጅግ ፈጣን እንደሆነ የጠቆመው ወጣቱ፤ ኢትዮ ኮደርስ ትውልድ በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ከሚፈጠሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ራሱን በፍጥነት ማራመድ እንዲችል የሚያደርግ ሥልጠና መሆኑን አመልክቷል፡፡
ስልጠናው እንደ ሀገር ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁኔታውን መሸከም የሚችል የዳበረ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል በማፍራትም የሚያበረክተው አስተዋፅዖ የጎላ መሆኑን አስረድቷል፡፡
በሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የኢትዮ ዲጂታል ኮደርስ አሰልጣኝ ወጣት ኢድሪስ ሰፋ በበኩሉ በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂው ህይወትን በማቃለል በተሳለጠ መልኩ ተሳትፎ እንዲኖርና ተጠቃሚነት እንዲጎለብት እያስቻለ ይገኛል ብሏል።
በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አማካኝነት ወጣቶችን በዘርፉ ያላቸውን አቅም ለማሳደግና ማብቃት የማሰልጠንና ከቴክኖሎጂው ጋር የማስተዋወቅ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቅሷል።
ስልጠናው በተለይ ዲጂታልና ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን በመረዳትና በመጠቀም ከጊዜው ጋር እኩል ለመራመድ እንደሚያግዝ ጠቅሶ፤ ይህም ሀገርን በዲጂታል ቴክኖሎጂው ዓለም የደረሰበት ደረጃ ማድረስ የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጸው።
አዲስ አበባ ፤የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተገልጋዮች ፋይዳ መታወቂያን ተጠቅመው በዲጂታል አማራጭ ትኬት የሚቆርጡበት አሰራር ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 03/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የለማ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮችንና የጭነት ባለቤቶችን የሚገናኝ መተግበሪያ አስጀምሯል። ...
Feb 12, 2025