የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ ነው

May 6, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ።

’’አርብቶ አደሮችና ትምህርት’’ በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ዛሬ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።


በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በኮንፍረንሱ እንደገለጹት፣ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማስፋፋት በሰራቸው ተግባራት ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በቀጣይም የተጀመሩ ኢንሼቲቮችና ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር ቀጣይነት ያለው ልማት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በማህበራዊ ልማት በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህ ረገድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማውጣት ለፖሊሲ ግብዓት እንዲውሉ ሲያከናውኑ የቆዩትን ስራዎች ማጎልበት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ለልማት እንዲውል በምርምር በማገዝ የአርብቶ አደሩ ሕይወት እንዲለወጥ በማድረግ በኩል የላቀ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማሳደግ የሚያግዙ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።


የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን በአካባቢያቸው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ወደ ልማት የሚቀየርበትን አቅም በምርምር እንዲያግዙ ጠይቀዋል።

ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስም በቀጣይ ለሚወጡ ሀገራዊ የልማት ፖሊሲዎች ጠቃሚ ግብዓቶች ለማፍለቅ ያግዛል ብለዋል።


የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን የአካባቢው ማህበረሰብ ሕይወት እንዲለወጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመድረኩ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ተጨማሪ ግብዓቶችና ተሞክሮዎችን እንደሚያገኝም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀዋሳ ከተማን ፈጣን እድገት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ሀዋሳ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሀዋሳ ከተማን ፈጣን እድገት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳ...

May 20, 2026

በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ ቀርቧል  

ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...

Apr 24, 2026

የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂ የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ ነው

ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...

Apr 22, 2026

ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካውያን በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...

Apr 15, 2026