🔇Unmute
ደብረ ማርቆስ ሚያዚያ10/2018 (ኢዜአ)፦በምስራቅ ጎጃም ዞን በመጪው ክረምት ሚተከሉ ከ916 ሺህ በላይ የቡና ችግኞች መዘጋጀታቸው ተገለፀ።
በዞኑ ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትባለሙያ አቶ ተሾመ በላይ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ በመጪው የክረም ወር ከ320 ሄክታ በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚተከሉ 916 ሺህ የቡና ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
በዋናነትም የአካባቢውን ስነ ምህዳርና የአየር ንብረት ተስማሚነት በማረጋገጥ ለቡና ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በቡና ልማቱምከ25 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ከ320 ሄክታር በላይ መሬትን ለመሸፈንዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
ችግኞቹ በመንግስት፣ በማህበራትና በግለሰቦች የችግኝ ጣቢያዎች ፈልተው የተዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅትም አርሶ አደሩን በተለያዩ የግብርና አማራጮች በማሳተፍ የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ እንዲችል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።
በዞኑ በደብረ ኤሊያስ፣ በማቻከልና በጎዛምን ወረዳዎች በኩታ-ገጠም እየተካሄደ ያለውን የቡና ልማት በማጠናከር በቀጣይ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ የማድረግ ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በማቻከል ወረዳ የውላ ቀበሌ ነዋሪአርሶ አደር አብነት ይርዳው፤ ቡናን በኩታ ገጠም ለማልማት ከግማሽ ሄክታር በላይ መሬት እያዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዚሁ ቀበሌ ነዋሪአርሶ አደር ገነት አያሌው በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ካለሙት ቡና እያገኙ ያለውን ጥቅም ለማስፋት በክረምቱ የሚተከልከሩብ ሄክታር በላይ ማሳቸውንእያዘጋጁመሆናቸን ገልጸዋል።
ለዚህም ከ6 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን ማፍላታቸውን ጠቁመውከራሳቸው የሚተርፈውን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አቅደው እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።
በዞኑ ባለፉት ዓመታት በተደረገ ጥረት ከ5 ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት በቡና መልማቱን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ሀዋሳ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሀዋሳ ከተማን ፈጣን እድገት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳ...
May 20, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...
Apr 24, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...
Apr 15, 2026