🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦የቅርስ ልማት እና ጥበቃ ስራ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል የአሰራር ስርዓት እንዲገባ እየተደረገ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እንዳስታወቀው፤ ሶስተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከሚያዝያ 13 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
የመጀመሪያው የቅርስ ምርምር ጉባዔ በ2016 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም የተስተናገደው ሁለተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከተለያዩ አገራት የተወጣጡ ምሁራን ጥናታዊ ጹሁፎች ያቀረቡበት እንደነበር ተገልጿል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ ሁለቱ ጉባዔዎች ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ሀገርነቷን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የዘንድሮው የቅርስ ምርምር ጉባዔውም "የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን" በሚል መሪ ሃሳብ ሚያዝያ 13 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሔድ ጠቁመዋል፡፡
የምርምር ጉባዔው በቅርስ ልማት ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት፣ አዳዲስ እውቀቶችን ለመለዋወጥ እና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህ የምርምር ጉባዔ ላይ 13 አዳዲስ የምርምር ጹሁፎች እንደሚቀርቡ ተናግረው፤ ጉባዔው የሚካሄደው በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ መሆኑን አስታውቀዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት ቅርሶች ለአገር ኢኮኖሚ እድገት ጉልህ ድርሻ እያበረከቱ ይገኛሉ።
የቅርስ አሰባሰብን፣ አመዘጋገብንና የሙዚየም አገልግሎትን ለማዘመን በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የቅርስ አሰባሰብ፣ አመዘጋገብ እና አያያዝ ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ሀዋሳ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሀዋሳ ከተማን ፈጣን እድገት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳ...
May 20, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...
Apr 24, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...
Apr 15, 2026