የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አዲስ የልማት ምዕራፍ ከፍቷል

Apr 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አዲስ የልማት ምዕራፍ መክፈቱን የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።

በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተመዘገቡ ስኬቶች ከአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣሙ ናቸው

የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፉት 18 ወራት የተከናወኑ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ውጤታማነት የሚገመግም ዝርዝር ሪፖርት ይፋ አድርጓል።


በሪፖርቱ መሠረት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት እያሳዩ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የወጪ ንግድ ገቢ በማሳደግ ረገድ እንዲሁም በሌሎችም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ማሻሻያው በኢትዮጵያ አዲስ የልማት ምዕራፍ የከፈተና ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡበት መሆኑን ገልጸዋል።

ሪፖርቱ በኢኮኖሚ ማኔጅመንት ቡድን አማካኝነት በራስ አቅም የተዘጋጀ መሆኑ በአሁኑ ወቅት በተቋማት ውስጥ ጠንካራ አቅም ያላቸው ባለሙያዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የመንግሥት ተቋማት የፖሊሲ ነጻነት ያላቸው መሆኑ ለማሻሻያው ስኬታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል።

ብሔራዊ ባንክ ትልቅ እመርታ እና የፋይናንስ ሥርዓቱን ጤናማነት ለማረጋገጥ አመርቂ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባንኩ የዋጋ ማረጋጋት እና የፋይናንሻል ዘርፉን ጤነኛነት ለመጠበቅ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ሪፖርቱ እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን ብቻ ሳይሆን፣ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትንም በዝርዝር ማካተቱን ጠቅሰዋል።

የአምራች ሴክተሩ እንዲነቃቃ እና ለሀገር ኢኮኖሚ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሀገር በቀል ሪፎርሙ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልፀው፥ ሪፖርቱ የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትክክለኛ አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀዋሳ ከተማን ፈጣን እድገት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ሀዋሳ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፡- የሀዋሳ ከተማን ፈጣን እድገት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳ...

May 20, 2026

በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ ቀርቧል  

ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...

Apr 24, 2026

የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂ የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ ነው

ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...

Apr 22, 2026

ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካውያን በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...

Apr 15, 2026