🔇Unmute
ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ):- የወላይታ ልማት ማህበር በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በከተማ ልማት እንዲሁም በሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ ተግባር እያከናወነ መሆኑ ተመላከተ፡፡
የወላይታ ልማት ማህበር "ሁለንተናዊ ልማት ለህዝባችን ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የገቢ ማሳባሰቢያ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የወላይታ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንደገለፁት፤ የልማት ማህበሩ በማህበራዊና ሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ ተግባር እያከናወነ ነው።
የልማት ማህበሩ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በከተማ ልማት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
የልማት ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአውቶሞቲቭ ጋራዥን ጨምሮ 11 ፕሮጀክቶችን አስገንብቶ ወደ ስራ በማስገባት በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በተለይ አቅመ ደካማ ወገኖችን በመርዳትና የመማር ዕድል ያልገጠማቸው ወገኖችን በማስተማር የልማት አጋርነቱን ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም በየአካባቢው ያለውን ፀጋ ወደ ልማት በመቀየር የህዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል አቅም መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥም በተደራጀ መልኩ ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችለውን ስትራቴጂክ እቅድ ነድፎ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር አጭር የጽሁፍ መልዕክትና የቴሌ ብር አካውንት አማራጭን ተግባራዊ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በተጀመረው 650 ሚሊዮን ብር የመሰብሰብ ልዩ ዕቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ 50 ሚሊዮን ብር ሊሰበሰብ መቻሉንም አመልክተዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የልማት ማህበሩ የበላይ ጠባቂ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው የልማት ማህበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከመንግስት ጋር በመተባበር በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የተማረ የሰው ኃይልን በማፍራት ግንባር ቀደም የሆነውን ማህበር ለማጠናከር የዞኑ አስተዳደር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ልማት ማህበሩ የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ በትምህርት፣ በጤና እንዲሁም በሰው ሀብት ልማት ላይ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የገለጹት ደግሞ የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አበባየሁ ቶራ (ዶ/ር) ናቸው።

ይህንን ተግባር በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በተለያዩ አማራጮች የተጀመረውን የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም አባላትና አጋሮች እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025