🔇Unmute
ሰመራ፤ የካቲት 25/2018(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ዜጎች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችል የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ዓሊ ተናገሩ።
ፋይዳ መታወቂያን ከተለያዩ አገልግሎቶች ጋር ማስተሳሰር ከተጀመረ ወዲህ የተመዝጋቢዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞ ቀጣይ 5 ዓመታት የሚመራበትን ''ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ'' በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራ በሁለንተናዊ ዘርፍ በተለይም የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ አጋዥ ሚና ይኖረዋል።
በዚህ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ዓሊ እንዳሉት ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ስርዓቱን ለማዘመን እያገዘ ነው።
ዘመኑ ያፈራውን የዲጂታል አሰራር እውን በማድረግ በቀላሉ መግባባት፣ መረጃዎችን መቀባበልና በተለይም የግብይትም ሆነ ሌሎች አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማግኝት እንደሚረዳ ነው የገለጹት።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማፋጠንና ከዘርፉም ቀጣይነት ባለው መልኩ ተጠቃሚ መሆን ያስችላል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የስማርት ሲቲ ግንባታን ጨምሮ በየደረጃው ዲጂታል አሰራር በመተግበር እየታዩ ያሉ ለውጦች የሚያበረታቱ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም ገልጸዋል።
ስትራቴጂው መረጃዎችን በቀላሉ የመመዝገብ፣ የማስቀመጥና የመለዋወጥ ስራን ቀላልና ፈጣን ማድረጉንም ለአብነት አንስተዋል።
በዋናነት የመንግስት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ጥራት ያላቸው በማድረግ በኩል ሰፊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025