🔇Unmute
ባህር ዳር ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦ በሕገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ንብረትን ለመንግሥትና ለሕዝብ ለማስመለስ የሚያስችለው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ዜጎች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን የእኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑ ተመላከተ፡፡
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የንብረት ማስመለስ አዋጅን ተግባራዊ በማድረግ የሕግ-የበላይነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሀገሩ ልማት ላይ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርግበትን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
በአማራ ክልል በሕገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ንብረትን ለመንግሥትና ለሕዝብ ለማስመለስ የሚያስችለውን የንብረት ማስመለስ አዋጅ ቁጥር 1364/2017 ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
ቢሮው በሕገ-ወጥ መንገድ ንብረት ያካበቱ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ ማስመለስ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ብርሃኑ ጎሽም እንደገለጹት፣ ይህ አዋጅ ዜጎች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን የእኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው።
አዋጁ ግለሰቦች በሕጋዊ መንገድ ብቻ ሀብት የማፍራት ባህል እንዲያዳብሩ በማድረግ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ይቀንሳል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ የአዋጁ ትግበራ የዜጎችን የገቢ ልዩነት በማጥበብ ለዘላቂ ሰላምና ደህንነት መሰረት የሚጥል መሆኑን አንስተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው በበኩላቸው፣ አዋጁ በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

አዋጁ ወንጀለኞችን በእስር ከመቅጣት ባለፈ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ያካበቱትን ንብረት እንዲመልሱ የሚያስገድድ መሆኑንም አመልክተዋል።
ያለአግባብ የተዘረፈና የተከማቸ ሃብትን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ጠቅላይ መምሪያው ከፍትህ ቢሮና ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ይህም የዜጎችን የገቢ ልዩነት በማጥበብና ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችልም አመልክተዋል።
የንብረት ማስመለስ አዋጅ በሙስናና በተለያዩ ሕገ-ወጥ ተግባራት የተከማቸ ሀብት ለልማትና ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል ለማድረግ መውጣቱ ይታወሳል።
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025