የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በባህር ዳር ከተማ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዘመናዊ የህዝብ ማጓጓዣ አውቶቡሶች ሥራ ጀመሩ

Jan 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፣ጥር 9/2018(ኢዜአ)፦የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዘመናዊ የህዝብ ማጓጓዣ አውቶቡሶችን ሥራ አስጀመረ።

ዛሬ የአውቶቡሶቹ ርክክብ ሥነ ስርአት የተካሄደው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣የምስራቅ እዝ ዋና አዛዥና የቀጠናው የፀጥታ ግብረ ሃይል ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል መሀመድ ተሰማና ሌሎች ሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በዚህ ወቅት እንደገለጹት፦ የከተማዋን ዘመናዊነት ከሚያረጋግጡ ተግባራት መካከል ዘመናዊና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት አንዱ ነው።

በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ዘመኑን የዋጁና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አስር አውቶብሶችን በመግዛት ዛሬ ሥራ ማስጀመሩን ገልፀዋል።


ይህም የከተማዋን ህዝብ የትራንስፖርት ችግር ከመፍታት ባለፈ የቱሪዝም ማዕከልና የኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማ ለማድረግ የተጀመረውን ሥራ እንደሚያጠናክር አስረድተዋል።

በተለይም አውቶቡሶቹ በከተማዋ በኮሪደር ልማት ከተገነባው ሰፊ የአስፋልት መንገድ ጋር የተጣጣመ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዘመኑን የሚመጥንና በአነስተኛ ክፍያ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ወሳኝና የከተማ እድገት መገለጫ እንደሆኑም አመልክተዋል።

በከተማዋ ከዚህ ቀደም ከ20 በላይ አውቶብሶች ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ጠቁመው፣ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች መጨመር የባህር ዳርን ስማርት ከተማነት ለማረጋገጥ የተያዘው ግብ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል።

የቢኬጅ (በላይነህ ክንዴ ግሩፕ) ባለቤትና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይነህ ክንዴ በእለቱ እንደገለጹት፥ ቢኬጅ እንደሀገር በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ያለ ድርጅት ነው ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት የተሰጠውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለማሳካትም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስገባት ጭስ አልባና ለብዙ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶችን በመገጣጠም እያከፋፈለ ይገኛል ብለዋል።

አውቶቡሶቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንደመሆናቸው መጠን ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ መሳካት ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸው፣ በሀገር ውስጥ መመረታቸው መለዋወጫ በቀላሉ ለማግኘት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በአውቶቡሶቹ ርክክብ ላይ የተገኙት አማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን አውቶብሶች ሥራ አስጀምረዋል።

በሥነ-ስርዓቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና የከተማዋ ነዋሪዎችም ተገኝተዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025