🔇Unmute
ደብረማርቆስ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ9 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የአስተዳደሩ ሥራና ስልጠና መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ሃላፊ አቶ መኮንን ሙሉአዳም ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአካባቢውን የልማት ጸጋ በመጠቀም ወጣቱን በተለያዩ የሥራ ዕድል አማራጮች ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
በዚህም በበጀት ዓመቱ ለ18ሺህ 500 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ በግማሽ ዓመቱ ለ9ሺህ 300 ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ ከ700 በሚበልጡ ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸውን ገልጸው በተሰማሩበት የከተማ ግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የአገልግሎት ዘርፍ ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን አመልክተዋል።

በበጀት ዓመቱ የሥራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች በመንግስትና በማህበረሰቡ ትብብር ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የመስሪያና የመሸጫ ሼዶችን በማስገንባት ለማስረከብ እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል።
በእስካሁኑም 66 የመስሪያና የመሸጫ ሼዶች ለኢንተርፕራይዞቹ መከፋፈላቸውን ገልጸው በበድር አቅርቦት በኩልም 4 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ለማሰራጨት ተችሏል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በከተማ ግብርና በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ለተሰማሩ ወጣቶች ከ11 ሄክታር በላይ መሬት መቅረቡን ተናግረዋል።
የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑት ወጣቶች መካከል የቀበሌ 09 ነዋሪ ወጣት ሁነኛው ዋሴ ከአምስት ጓደኞቹ ጋር በከብት ማድለብ ሥራ በመሰማራት ገቢያቸውን ለማሳደግ እየተጉ መሆኑን ገልጿል።
ወጣት ምዕራፍ ይበልጣል በበኩሏ ከጓደኞቿ ጋር በመደራጀት በዶሮ እርባታ ዘርፍ እንደተሰማሩ ገልጻ በመጀመሪያ ዙር ያሳደጓቸውን የሥጋ ዶሮዎችን በመሸጥ ከ70ሺህ ብር በላይ ትርፍ ማግኘታቸውን ገልጻለች።

በአሁኑ ወቅትም ከ2ሺህ በላይ እንቁላል ጣይ የዶሮ ጫጩቶችን በመረከብ ተንከባክበው እያሳደጉ መሆኑንና በቀጣይ የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን ተግተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከሦስት ጓደኞቿ ጋር በመደራጀት በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ ሀብት እያፈሩ መሆናቸውን የገለፀችው ደግሞ የቀበሌ 05 ነዋሪ ወጣት መቅደስ ደጉ ናት።
የመምሪያው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ከ17 ሺህ 600 ለሚበልጡ ወጣቶች በተለያየ መስክ የሥራ ዕድል መፈጠሩ ታውቋል።
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025