የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ  መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ቅንጅታዊ አሰራር ይጠናከራል

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያሉትን ተግዳሮቶች በመፍታት በዘርፉ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚጠናከር ተገለጸ።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመሠረተ ልማት ክላስተር የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ዛሬ በአዳማ ተካሂዷል።

በዚህ ወቅት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) እንዳስታወቁት በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር የተያያዙ ናቸው።


በዚህም ምክንያት የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች የአቅማቸውን ያህል እያመረቱ እንዳልነበር ተናግረዋል።

ይህን ችግር ለመፍታት እንደ ሀገር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በመፍጠር በኢንዱስትሪ ዘርፍ በአጭር ጊዜ መሠረታዊ የሆኑና ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።

ይህንን የበለጠ ለማሳለጥ እንዲቻልም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመሠረተ ልማትን ጨምሮ ስድስት ክላስተሮች ተቋቁመው በየደረጃው በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት የአምራች ኢንዱስትሪ ማነቆዎችን በመለየት እንዲፈቱ እገዛ ማድረጋቸውን አንስተዋል።

ይህም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ በሀገር ውሰጥ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአቅማቸው ልክ ማምረት እንዲችሉ እና ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ እንዲችሉ ያደርጋል ብለዋል።

እንዲሁም አምራች ኢንዱስትሪው አገር የምትጠብቀውን ውጤት እንዲያስመዘግቡና በዘርፉ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ምቹ መደላድል እየተፈጠረ እንደሚገኝ አውስተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የሚኒስትሩ ተወካይ አቶ ዮናስ መኩሪያ በበኩላቸው፤ አምራች ኢንዱስትሪውን ለማጠናከርና ለማስፋፋት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የተቀናጀ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


በቅንጅታዊ አሰራር መፍትሄዎችን በመስጠት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ የሮሰን ኪሲ፣ ክላስተሩ ባለፉት ስድስት ወራት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች መሰረተ ልማት አቅርቦትን ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸዋል።


ለ176 ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል፤ ለ522 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ አነስተኛ ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም አውስተዋል።

እንዲሁም በስምንት ክልሎች 23 ሺህ ሄክታር መሬት ለኢንዱስትሪ ተከልሎ ለአልሚዎች እየተላለፈ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

አምስት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከዋናው መንገድ ጋር ለማገናኘት እና በተለያዩ አካባቢዎች ግንባታቸው እየተካሄዱ ለሚገኙ ሶስት ደረቅ ወደቦች ክትትልና ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።


ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ደሴ አስማረ ፤ ለአምራች ኢንዱስትሪው ክላስተር ተቋቁሞ በቅንጅት መሰራቱ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃት እና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ምቹ መደላድል መፍጠሩን አውስተዋል።

ከመድረኩ ጎን ለጎን ተሳታፊዎቹ የአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025