የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ነው 

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 29/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት መርሃ ግብር ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽነር ሳንዶካን ደበበ ገለጹ።

የኢትዮጵያን የኒውክሌር ኃይል ልማት መርሃ ግብር ማስጀመሪያና የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ሥራ ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረክ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽነር ሳንዶካን ደበበ፣ የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭና የባለድርሻ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽነር ሳንዶካን ደበበ ፤ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት የኃይል ደህንነትን በማረጋገጥ የኢኮኖሚያዊ ሽግግርና የረጅም ጊዜ የመቋቋም አቅም ግንባታ ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ የልማት ተነሳሽነት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ንጹህ የኃይል አቅርቦት የማመንጨት አቅምን በማላቅ በጤና፣ ግብርና፤ በኢንዱስትሪ እና የምርምር ትግበራ ማዕቀፍ የተቃኘ መሆኑን ገልጸዋል።

የሰላማዊ አማራጭ የኒውክሌር ሳይንስ ልማት መርሃ ግብሩ ዓላማ የኢትዮጵያዊያንን ህይወት በተጨባጭ የሚያሻሽሉ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ዕድል ማረጋገጥ እንደሆነም ተናግረዋል።


የኃይል አቅርቦት የዕድገት ሞተር ነው ያሉት ኮሚሽነሩ የሰላማዊ አማራጭ አስተማማኝ የኒውክሌር ኃይል ልማት መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ዕድገት ጥራትና ፍጥነት ይቀርፃል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የኒውክሌር ኃይል ልማት ቁርጠኝነት ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትን ማረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ ደፋር ውሳኔ መሆኑን አብራርተዋል።

በ​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ በጉባ ከተበሰሩ ማግስት በሩሲያ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል መድረክ ድረስ ኢትዮጵያ ለሰላማዊ የኒውክሌር ልማት ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን አስታውሰዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ ለመጠቀም ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነች ብለዋል።

​የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን በተሰጠው ግልጽ ሥልጣንና ጠንካራ መዋቅር ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

​የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የተፈጠረው የሥልጠና ፕሮግራምና የባለሙያ የልምድ ልውውጥ፣ ክህሎት ግንባታና የቴክኒክ ትብብር እየተሳለጠ መሆኑን ተናግረዋል።

​በቀጣይም ኢትዮጵያ በዕውቀትና በሰላማዊ የኒውክሌር ልማት የጋራ ርዕይ በመመስረት ከዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የትብብር ስራን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026