🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ):- በባለሃብቶች ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ በመሰጠቱ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር ማስቻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
በሂደት ከተመለሱ ጥያቄዎች መካከል 14 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች መቀየር መቻሉ አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ መሆኑን አስረድተዋል።
እንዲሁም ከውጭ ምንዛሪ ጋር ተያይዘው ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች በኢኮኖሚ ማሻሻያው መሠረት ለውጦች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻዎችን ማስፋቱ ድርጅቶች በቀላሉ ምርታቸውን ወደ ተለያዩ ሀገራት መላክ እንዲችሉ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ላይ የጎላ ሚና አበርክቷል ብለዋል።
በኮሚሽኑ የሚሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ፈጣን፣ ግልጽና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን አመላክተዋል።
በአጠቃላይ በዘርፉ በተደረጉ ዘርፈ-ብዙ የማሻሻያ ሥራዎች በእ.ኤ.አ 2024/2025 ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማስመዝገብ መቻሉን ለኢዜአ አረጋግጠዋል።
ኢንቨስትመንት በይበልጥ እንዲስፋፋና እንዲነቃቃ ኮሚሽኑ የተለያዩ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ለአብነትም ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለማስተዋወቅ የሚያስችል የአምስት ዓመት የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ በማውጣት ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል።
ቀደም ሲል የነበረውን ስትራቴጂ ወደ ኢላማ ተኮር የኢንቨስትመት ማስተዋወቅ ሥራ በመቀየር ከሌሎች ተቋማት ተግባራት ጋር በቅንጅት እየተሠራበት እንደሚገኝም ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026