የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢንቨስትመንት ከባቢውን ምቹ ያደረጉ የማሻሻያ ተግባራት ተከናውነዋል

Dec 2, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢንቨስትመንት ከባቢውን መቀየር ያስቻሉ በርካታ ስኬታማ ማሻሻያዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዐቅም ለማሳደግ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተነድፎ ዓይነተ-ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከሚያተኩርባቸው ዘርፎች አንዱ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ፍሰት በይበልጥ ማሳደግ መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህም የኢንቨስትመንት ምኅዳሩን ለማሻሻል የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውን ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።

ከነዚህ መካከል የሕግ ማሻሻያ በማድረግ የኢንቨስትመንት ከባቢውን ተገማች እና ግልጽ ወደሆነ የኢንቨስትመንት ዐውድ ለመቀየር ያስቻሉ ከ120 በላይ የሕግ ማሻሻያዎች ተደርገዋል ብለዋል።

ማሻሻዎቹን ተከትሎም ለበርካታ ዓመታት ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ የነበሩ ሴክተሮችን ክፍት በማድረግ እንዲሳተፉበት ተደርጓል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገው ጥረት ተሳክቶ አባልነቷ ሲረጋገጥ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን በይበልጥ እንደሚያሳድገው አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም በቅርቡ ወደ ተግባር የገባው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ማደግ የጎላ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026