🔇Unmute
ከሚሴ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦ በተያዘው ዓመት በበጋ መስኖ ስንዴ ከ4 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት እንደሚለማ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የአማራ ክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ የበጋ መስኖ ስንዴ የዘር ስራን ዛሬ አስጀምረዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በማስጀመሪያው ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለፁት፣ እንደ ሀገር በዘንድሮው ዓመት ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት የዘር ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በሜካናይዜሽን በታገዝ መንገድ ከሚለማው የመስኖ ልማት ከ175 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።
አስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴም ከ1 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን አስረድተዋል።

የስንዴ ልማቱን ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና ለውጭ ገበያ የማቅረብ ተግባር በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ለዚህም ከዚህ ቀደም በስንዴ ለምቶ የማያውቅ መሬትን ወደ ልማት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ዛሬ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እየተካሄደ ያለው የበጋ መስኖ ስንዴ ዘር ስራም የዚሁ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በክልሉ ከ350 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት እየተሰራ ነው።

ከመስኖ ልማቱ ከ13 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመው፤ ምርታማነትን ለማሳደግ የግብዓትና የቴክኖሎጂ አቅርቦት እየተደረገ ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በወቅቱ እንደገለፁት፣ የመስኖ ልማቱን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት እየተሰራ ነው።

በዚህም በተያዘው የበጋ ወራት ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል ለማልማት ታቅዶ የዘር ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።
ለአርሶ አደር ቴክኖሎጂ እና ግብዓት በማቅረብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ምርቱን ለገበያ እንዲያቀርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026