🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፦ የማሌዢያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የሚጠቀሙበት ምቹ ምኅዳር መኖሩን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው ፎረም ላይ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የንግድና ኢንቨስትመንት አልሚ ባለሃብቶች ተገኝተዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር በማጠናከር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጎልበት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያና ማሌዢያ ያሏቸው ብዝኅ ሕብረ ብሔራዊነትን የተላበሱ የጋራ እሴቶች ለጋራ ዕድገትና ቀጣናዊ ትብብር ልዩ ዕድል መሆናቸውንም ገልጸዋል።
እ.አ.አ በ1965 የተጀመረውን የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ፕሬዝዳንት ታዬ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የኢንቨስትመንት ሥነ-ምኅዳር መገንባቷን አስረድተዋል።
በግብርና መስክም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትክክለኛው የልማት መንገድ ላይ እየተጓዘች እንደምትገኝ ፕሬዝዳንት ታዬ አብራርተዋል።

በዚህም ሁለቱ ሀገራት በግብርና፣ በእንስሳት፣ በማዕድንና በሌሎች ወሳኝ የልማት መስኮች ያላቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
የማሌዢያ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች በመጠቀም የጋራ ብልጽግና እና ተጠቃሚነትን የሚወስን የልማት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ማሌዢያ ከዲፕሎማሲ ባለፈ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነቷን ለማስፋት እያከናወነች ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።
የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የሀገራቱን ሁለንተናዊ ትብብር ለማጠናከር ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026