🔇Unmute
ሀዋሳ ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተክሌ ጆንባ አስታወቁ።
ሀዋሳ ከተማ የፍቅር ሀይቅ፣ ታቦርና አላሙራ ተራራን የመሳሰሉ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን በውስጧ ይዛለች።
ከተፈጥሯዊ መስህቦቿ ባለፈ ባህላዊና ሀይማኖታዊ በዓላት የሚከበሩባት መሆኗ በጎብኚዎች ተመራጭ አድርጓታል ።

ይህን የከተማዋን ቱሪስት መስህብነት የኮሪደር ልማትና ሌሎች የጉብኝት መዳረሻዎች ልማት እያሳደገው ነው።
ለአብነትም የታቦር ተራራን ለመዝናኛና ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ተጠናቀው በቅርቡ በከፊል ክፍት ተደርገዋል።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራት ሀዋሳ ከተማን ለጎብኚዎች ተመራጭ ማድረግ ተችሏል።
የከተማዋን የኮሪደር ልማት ግንባታና የታቦር ተራራን በማልማት ምቹ በማድረግ የጎብኚዎችን ቁጥር በመጨመር የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በታቦር ተራራ ላይ የእረፍት ጊዜያቸውን በመዝናናት ሲያሳልፉ ያገኘናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት የታቦር ተራራ መዝናኛ ስፍራ ልማት ለከተማዋ የቱሪስት ፍሰት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባለፈ ለስፖርት እንቅስቃሴ የጎላ ድርሻ አለው።

ነዋሪዎቹ ታቦር ተራራ ለሀዋሳ ከተማ ልዩ ውበት መሆኑን ገልፀው የተጀመረው ፕሮጀክት ተጠናቆ ለጎብኚዎች ክፍት በመደረጉ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የታቦር ተራራ ልማት ለከተማዋ ነዋሪዎች ተጨማሪ የመዝናኛ ስፍራን መፍጠሩንም ነው የተናገሩት።
ስፍራውንም በማስፋፋት ለከተማዋ ገቢ የድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ እንደሚገባም አመልክተዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026