🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ)፦ የኩዌት ፈንድ ለኢትዮጵያ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) አመታዊ ስብሰባ ላይ በዋሺንግተን ዲሲ መካሄዱን ቀጥሏል።
በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዓመታዊው ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አማካሪ ተክለወልድ አጥናፉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
አቶ አህመድ ሽዴ ከውይይቱ ጎን ለጎን ከኩዌት ፈንድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጀነራል ዋሊድ አል-ባሃር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ እና የኩዌት ፈንድ የረጅም ጊዜ አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች፣ ፈንዱ በኢትዮጵያ እየደገፋቸው ያሉ ፕሮጀክቶች፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የልማት የትኩረት መስኮችና እድሎች እንዲሁም ፈንዱ በኢትዮጵያ ያለውን ተሳትፎ ማሳደግ በሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተደርጓል።
አቶ አህመድ ሽዴ በውይይቱ ወቅት የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ጥረቶች እና ቁልፍ የልማት መስኮች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።
የእዳ ሽግሽግ ሂደት፣ የግሉ ዘርፍ ልማትና የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ በማሳያነት የጠቀሱት ሚኒስትሩ በእነዚህ መስኮች የፈንዱ ድጋፍ ቁልፍ መሆኑን አመልክተዋል።
ከሁለቱ ወገኖች አበይት የውይይት ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያን አዲስ ዓለም አቀፍ ግዙፍ አየር ማረፊያ በፋይናንስ መደገፍ የሚቻልበት መንገድ ይገኝበታል።
የኩዌት ፈንድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጀነራል ዋሊድ አል-ባሃር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ራዕይ እና የሪፎርም አጀንዳው ጅምር ስኬቶችን አድንቀዋል።
የኩዌት ፈንድ የኢትዮጵያን ልማት በተለይም ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችና ሌሎች ቁልፍ መስኮችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ዋሊድ በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ለሚደረጉ የልማት ፋይናንስ ድጋፎችን ከሚያስተባብረው " አረብ ኮርድኔሽን ግሩፕ" ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰው ይህሞ የአረብ የፋይናንስ ተቋማት የጋራ ትብብር እንደሚያጎለብትና ሀብትን በተቀናጀ መልኩ ማሰብሰብ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ሁለቱ ወገኖች አጋርነታቸውን ለማጠናከር የተስማሙ ሲሆን የኩዌት ፈንድ ለኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊና ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥ ለሚያመጡ የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ የበለጠ እንደሚያጠናክር የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከዓመታዊ ስብሰባው ጎን ለጎን ከበርካታ የባለብዙ ወገን ድርጅቶችና ተቋማት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026