🔇Unmute
አሶሳ፤ ጥቅምት 4/2018 (ኢዜአ)፦ በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ወደ ሌሎች የክልሉ ከተሞች የማስፋት ተግባር እንደሚጠናከር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በአሶሳ ከተማ በሁለተኛው ዙር የ12 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ መጀመሩም ተገልጿል።
የቢሮው ኃላፊ ሙሐመድ አልማሂ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ሳቢ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በዚህም በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ወደ ሌሎች የክልሉ ከተሞች ለማስፋት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም የኮሪደር ልማት ሥራውን በባምባሲ፣ በግልገል በለስ እና በካማሽ ከተሞች ላይ ለማከናወን የዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።
እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ በአሶሳ ከተማ ሁለተኛው ዙር የ12 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ ተጀምሯል።

የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫዎች በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች እንደሚከናወን አስረድተዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው የእግረኛ መንገድን፣ አረንጓዴ ቦታዎች እና የተለያዩ የመዝናኛ ማዕከላትን እንደሚያካትት ጠቅሰው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱን አስታውቀዋል።
ህብረተሰቡ በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ያሳየውን ትብብር አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥልና ለከተማዋ ልማት የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
ከዚህ በፊት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ውበት የጨመረ እና ለነዋሪዎች ምቹ መደላድል የፈጠረ በመሆኑ በሁለተኛው ዙር የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ተግባር የከተማዋን ገፅታ የበለጠ እንደሚቀይረውም ተናግረዋል።
በአሶሳ ከተማ በመጀመሪያው ዙር 9 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት መከናወኑ ይታወቃል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026