🔇Unmute
አርባ ምንጭ ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡-ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኃይል አቅርቦት ባለፈ በተፈጠረው የንጋት ሃይቅ የቱሪዝም ዘርፍ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
ላለፉት 14 ዓመታት የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመቋቋም በአትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ለምረቃ የበቃው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ባለፈ ለቀጣናው ሀገራትም ፀጋ ሆኗል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኃይል አቅርቦት ባለፈ በተፈጠረው የንጋት ሃይቅ የቱሪዝም ዘርፍ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ፋይዳው የጎላ ነው።
በተጨማሪም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገርን ብሎም የአፍሪካ አህጉርን በጎ ገጽታ በመገንባት ረገድም በጎ ሚና እንዳለውም አመልክተዋል።
ግድቡ በሀይል አቅርቦት ልማትን ለማፋጥን ካለው ጠቀሜታ ባለፈ በቱሪዝም ዘርፍ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅና የቀጣናው ሀገራትን ለማስተሳሰር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የዓለምን ቀልብ የሚስቡ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና ባህላዊ የቱሪዝም ሀብቶች እንዳሏት ገልጸው፣ የሕዳሴው ግድብም ለቱሪዝም ዘርፉ ተጨማሪ አቅም መሆኑን ምሁራኑ አንስተዋል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህር ሄኖክ በቀለ (ዶ/ር) እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሃይል ከማመንጨት ባለፈየንጋት ሃይቅ የቱሪዝም ዘርፉን የሚያነቃቃ ነው።

ይህም ለሀገር የኢኮኖሚ ጥቅም እንደሚያስገኝ ጠቅሰው፤ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠርና የንግድ እንቅስቃሴን በማሳለጥ ረገድ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
እንደ ሄኖክ (ዶ/ር) ገለጻ ግድቡ ከሀገር ባለፈ የአፍሪካ አህጉርን ገጽታ በመገንባት በኩል ጠቀሜታው የጎላ ነው።
ኢትዮጵያ የተለያዩ የቱሪዝም ሀብቶች እንዳሏት ገልጸው፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለዘርፉ መጠናከር ተጨማሪ አቅም እንደሚሆንም ተናግረዋል።
የህዳሴ ግድቡ ተገንብቶ መጠናቀቅ ከቱሪዝም ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የገለፁት ደግሞ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር አባይ ወርቁ ናቸው።

ግድቡ በአካባቢ ጥበቃ፣ በንግድ እንዲሁም ከጎረቤት ሃገራት ጋር የሚኖርን ትብብር ከማጠናከር አንፃር አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረውም መምህር አባይ አመልክተዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026