የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በድሬደዋ የኢንደስትሪዎችን አቅም በማሳደግ በተፈጠረው የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነናል -ወጣቶች

Oct 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬደዋ፣ መስከረም 30/2018(ኢዜአ)፡- በድሬደዋ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንደስትሪዎችን አቅም በማሳደግ በተፈጠረው የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ወጣቶች ተናገሩ።

የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ቡድን ትላንት በድሬዳዋ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ወደ ስራ የገቡ 11 የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ስራ ያስጀመሩ ሲሆን ኢንደስትሪዎቹ ከ1500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠራቸው በወቅቱ ተመላክቷል።

ተመርቀው ወደስራ በገቡ ኢንደስትሪዎች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምሩቃን ለኢዜአ እንደተናገሩት በኢንዱስትሪዎቹ በተፈጠረላቸው ይሰራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።

ከስራ ዕድል ተጠቃሚዎች መካከል በኢንጂነሪንግ የተመረቀው ወጣት አገኘሁ አለማየሁ እንደገለፀው፤ መንግስት የኢንደስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የቀየሰው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት የስራ እድሉ ተጠቃሚ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ታምርት ወደ ስራ የገባው የቆርቆሮ ፋብሪካ ለጀማሪዎች የስራ እድል በመፍጠሩ ለእሱና ለሌሎች ወጣቶች የስራ ዕድል መክፈቱን አክሏል።

በከተማዋ አዲስ በተከፈተው የዱቄት ፋብሪካ የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አቶ ምንዳ ኡርጌሳ፣ በድሬዳዋ የኢንደስትሪዎች መነቃቃት ለስራ ፈላጊውም ጭምር አስተዋፅኦ በማድረጉ ከስራ እድሉ ተጠቃሚ መሆኑን ጠቁሟል።

ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የተመረቀው ወጣት ሙርቴይሳ መሐመድ በበኩሉ በመንግስትና በባለሀብቶች ቅንጅት የተተገበረው የኢንቨስትመንት ማስፋፋት ለድሬዳዋ ዕድገት እና ለወጣቶች ተጠቃሚነት ወሳኝ እየሆነ መጥቷል ብሏል።

እሱም ይሄን እድል በመጠቀም በተማረበት ሙያ ወደ ስራ መግባቱን አስረድቷል።

''የማዳበሪያ ከረጢት ፋብሪካ ወደ ስራ መግባቱ ለእኔና ለብዙ ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥሮልናል'' ያለችው ደግሞ ወጣት ማርታ ዋቅጅራ ናት።

ከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለአገር ዘላቂ ልማትና ለስራ እድል ፈጠራ ተጨማሪ አቅም መፍጠሩን ተናግራለች።

የፋብሪካዎቹ ስራ መጀመርም የወጣቶች የስራ ዕድል ጥያቄን ለመመለስ እያገዘ መሆኑን ተናግራለች።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...

Mar 31, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅማችንን አሳድጓል- አምራች ኢንዱስትሪዎች

ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...

Mar 26, 2026