🔇Unmute
ወልዲያ፤ መስከረም 30/2018(ኢዜአ)፦ የወልዲያ ከተማና አካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 12ኛ ዓመት፣ 17ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን አካሂዷል።
ከምክር ቤቱ አባላት መካከል አሳዬ በላይነህ እና ደረበ አያሌው፤ በከተማ አስተዳደሩ የተያዙ እቅዶችን በመደገፍና ክትትል በማድረግ ለተፈፃሚነታቸው በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።
የወልዲያ ከተማና አካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም በቅንጅት መሰራት እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት አስገንዝበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ንጉስ ዝናቡ፤ በክረምቱ ህብረተሰቡንና አጠቃላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ያሰተፉ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
በዚህም መሰረት ከ54ሺህ 300 በላይ ሰዎች የተሳተፉባቸው የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ፣ በትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ማሟላትና ምቹ የማድረግ ስራ፣ የደም ልገሳ እና ሌሎችም አገልገሎቶች ተከናውነዋል ብለዋል።
በክረምቱ የታየው ጥሩ ጅምርና መልካም ተሞክሮን በመቀመር በበጋ ወቅትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026