🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ ከንግድ ቀጣናነት ባለፈ የአፍሪካ ዘላቂ ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ይታመናል።
የንግድ ቀጣና ስምምነቱ አፍሪካዊያንን የኢኮኖሚ በማስተሳሰር ፈጣንና ወደ ብልፅግና የሚያሻግር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማረጋገጥ ያስችላል።
የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ድህነትን ለመቀነስ ወሳኝ እንደሆነም ይገለጻል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተደረገውን ስድስተኛ ዙር የሥራ ቡድን ስብሰባ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን መጀመር የሚያስችል የሰነድ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በመጭው ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ በይፋ እንደምትጀምር አስታውቀዋል።
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026
ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...
Apr 3, 2026
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ...
Mar 31, 2026
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራ...
Mar 26, 2026