አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2017(ኢዜአ)፦ የጥናት ግኝቱ በአስር አመቱ የልማት እቅድ ትኩረት የተሰጣቸውን እንደ የግብርና ማቀነባቀር፣በፋርማሲቲካልና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች የበለጠ ተወዳዳሪና አካታች እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከአፍሪካ የኢኮኖሚ ለውጥ ማዕከል ጋር በመተባበር "የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ለውጥ እይታ" በሚል ርዕስ ያካሄደውን የጥናት ግኝት በተመለከተ ለመንግስት እና ለባለድርሻ አካላት የፖሊሲ ምክረ-ሀሳቦች አቅርቧል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃጽዮን በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በ2030 የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መር አቅጣጫ ተመስርታ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን እየሰራች ትገኛለች።
መንግስት ኢኮኖሚውን አካታችና ተወዳዳሪ እንዲሆን የፖሊሲ ለውጥ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ በጥናትና ምርምር ለማስደገፍ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ፀጋ በበኩላቸው፤ ጥናቱ ከሀገራዊ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አኳያ ኢትዮጵያ ያለችበት ደረጃ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል።
የሀገሪቱን እድገት ትራንስፎርም ከማድረግ አኳያ ምን ላይ ትኩረት ተደርጎ ቢሰራ የበለጠ ውጤት ሊያመጡ በሚችሉ ስራዎች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ ለፖሊሲ አውጪዎችና አስፈፃሚዎች ምክረ ሀሳብ ለመስጠት ያለመ ጥናት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በጥናቱ መሰረት ኢትዮጵያ በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በፋርማሲቲካልና በዲጂታል የኢኮኖሚ ዘርፎች ውጤታማ የሆነ አፈፃፀም እንዳላት ጠቅሰው፤ ይህም የበለጠ አጠናክራ ልትሰራ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚወጡ ፖሊሲና ስትራተጂዎች በጥናትና ምርምር ሊደገፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ከአፍሪካ የኢኮኖሚ ለውጥ ማዕከል የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን ኢንዴክስ ዋና የኢኮኖሚ አስተዳደር ብሬንዳ ቻንጎ ቻንዳ እንደሚናገሩት፥ ጥናቱ በዋነኝነት ሶስት ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በአግሮፕሮሰሲንግ፣ በፋርማሲቲካልና በዲጂታል የኢኮኖሚ ዘርፎች ይገኝበታል።
በዚህም ኢትዮጵያ በተለይም ባለፉት 20 አመታት በሶስቱም ዘርፎች ከሌሎቹ አፍሪካ ሃገራት አንፃር የተሻለ አፈፃፀም እንዳላት ገልፀው፥ ያንን አጠናክራ ልትቀጥል ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025